በYouTube ይፋዊ የአርትዖት መተግበሪያ YouTube ፍጠር ቪድዮዎችዎን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ይውሰዱ። በቀላሉ ታዳሚዎችዎን የሚማርኩ አስደናቂ ቪድዮዎችን ለመሥራት ማጣሪያዎች እና ተጽዕኖዎችን፣ ከቅጂ መብት ክፍያዎች ነፃ ሙዚቃን፣ ተደራቢ ድምፅን፣ ራስ-ሰር መግለጫ ጽሁፎችን እና ሌሎችን ያክሉ — ሁሉም የተወሳሰቡ የአርትዖት መሣሪያዎች ሳያስፈልጉ።
ቀላል የቪድዮ አርትዖት መሣሪያዎች
• በቀላሉ ቪድዮዎች፣ ፎቶዎች እና ኦዲዮን በአንድ ቦታ ያዋህዱ
• የቪድዮ ቅንጥቦችን ይከርክሙ፣ ይቀንጥቡ እና ይቁረጡ
• ቅንጥቦችዎን ያለ እንከን አንድ ላይ ለማዋሃድ ከ40 በላይ ሽግግሮች ውስጥ ይምረጡ
• ቪድዮዎን ያፍጥኑ ወይም ቀስ ያድርጉ
ቀጣይ ደረጃ የቪድዮ አርትዖት ባህሪያት
• አንድ ጊዜ ብቻ መታ በማድረግ ቪድዮችዎ ላይ መግለጫ ጽሁፎችን ወይም የግርጌ ጽሁፎችን በራስ-ሰር ያክሉ (በተመረጡ ቋንቋዎች የሚገኝ)
• በኦዲዮ ማፅጃ መሣሪያው የሚያዘናጋ የበስተጀርባ ድምፅን በቀላሉ ያስወግዱ
• በቆርጦ ማውጣት ተጽዕኖው የቪድዮዎን ዳራ ያስወግዱ
ሙዚቃ እና ኦዲዮ
• በሺዎች በሚቆጠሩ ከቅጂ መብት ክፍያዎች ነፃ የሙዚቃ ትራኮች እና የድምፅ ተጽዕኖዎች ቪድዮዎ ላይ ሕይወት ይዝሩበት
• በምት ማዛመድ የማጀቢያ ድምፅዎን ምት ያግኙ እና የቪድዮ ቅንጥቦችዎን ከሙዚቃው ጋር በቀላሉ ያስምሩ
• ተደራቢ ድምፅ በቀጥታ መተግበሪያ ውስጥ በመቅዳት ቪድዮዎችዎን ይተርኩ
ማጣሪያዎች እና ተጽዕኖዎች
• የቀለም ሙሌት፣ ብሩህነት እና ሌሎችን በማስተካከል ቀለሙን ያሻሽሉ
• በብጁ ማጣሪያዎች ስሜቱን ያቀናብሩ
• ቪድዮዎችዎ ጎልተው እንዲታዩ ለማድረግ ከበርካታ ተጽዕኖዎች ውስጥ ይምረጡ
ተለጣፊዎች እና ቅርጸ-ቁምፊዎች
• በመቶዎች በሚቆጠሩ ቅርጸ-ቁምፊዎች እና እነማ የጽሁፍ ተጽዕኖዎች የፈጠራ ችሎታዎን ያክሉ
• ከእርስዎ ቅጥ ጋር ለማዛመድ ከተለጣፊዎች፣ GIFዎች እና ስሜት ገላጭ ምስሎች ቤተ-መጽሃፍት ውስጥ ይምረጡ
ለመጋራት የተሠሩ
• በተለያዩ ቅርጸቶች ለማጋራት የቪድዮዎችዎን መጠን አግድም፣ የመሬት ገፅታ እና ኩብን ጨምሮ ወደ የተለያዩ ምጥጥነ ገፅታዎች ይቀይሩ
• በቀላሉ ቪድዮዎን በቀጥታ ወደ የYouTube ሰርጥዎ ይስቀሉ እና ፈጠራዎን ለታዳሚዎ ያጋሩ