[go: nahoru, domu]

Jump to content

ፓሪሲ

ከውክፔዲያ
የ17:12, 19 ጃንዩዌሪ 2023 ዕትም (ከSiren-Com (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የፓሪሲ ወርቅ እስታቴር
የፓሪሲ ወርቅ እስታቴር

ፓሪሲሴን ወንዝ አጠገብ (በአሁኑ ፈረንሳይ) በጥንት ቢያንስ ከ3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ጀምሮ እስከ ሮሜ መንግሥት ድረስ የኖረ የኬልቶች ብሔር ነበር።

60 ዓክልበ. ከሌላ ጎሣ ሱዌሲዮኔስ ጋራ በአለቃው ዌርኪንገቶሪክስ መሪነት የዩሊዩስ ቄሣርን ወረራ ተቃወሙ። ዩሊዩስ ቄሣርም እንደ ጻፈ ዋና ከተማቸው በሮማውያን ሥር ሉቴቲያ (የአሁኑም ፓሪስ) ሆነ። ከሮማውያን ቀድሞ ይህ ሥፍራ «ሉኮቶኪያ» ይባል ነበር።

ሌላ ፓሪሲ የሚባል ኬልቲክ ብሔር በአሁኑ እንግላንድ ይገኝ ነበር። የዚህ ብሔር ቅርንጫፍ መሆናቸው በሊቃውንት ተከራካሪ ነው።