[go: nahoru, domu]

Jump to content

የላንካስተር ውል

ከውክፔዲያ

የላንካስተር ውል1736 ዓም በአንዱ ወገን በቨርጂኒያሜሪላንድታላቅ ብሪታንያ ቅኝ አገራትና በሌላው የሆዴነሾኒ ተባባሪነት ወይም ስድስት ብሔሮች የተደረገ ውል ነበረ። ውሉ በአልባኒኒው ዮርክ ተፈጸመ። በዚህ ውል ከሆደናሾኔ ወይም ኢሮኳ ብሔር እና ከቅኝ አገሮቹ መሃል ያለው ወሰን ከበፊቱ ብሉ ሪጅ ተራሮች ጫፍ እስከ ኦሃዮ ወንዝ (በብሪታን ትርጓሜ) ወይም እስከ ኦሃዮ ወንዝ ተፍሳሽ (በኢሮኳ ትርጉም) ድረስ አስፋፋው። በኢሮኳ ዘንድ ሸናንዶዋ ሸለቆ ብቻ ለብር ዋጋ ሸጡ፤ በብሪታንያ ዘንድ ግን ኬንታኪና መላው ምእራብ ቨርጂኒያ ገዝተው ነበር።

ቤንጃሚን ፍራንክሊን የላንካስተር ውል አንብቦ ወደደውና ለቅኝ አገሮቹ ሁሉ በማሳተሚያ ቤት አሰራጨው። በውሉ ውስጥ ኢሮኳውያን አለቆች ለእንግሊዞች እንዳሉ «ሰዎች ከመቀመጫችሁ ተርቀው ምን እንደሚያደርጉ ልታውቁ መታሠብ አትችሉም» ብለዋል። አስተርጓሚው ኮንራድ ቫይዘር (ታቸረዋገን) ተባለ።