[go: nahoru, domu]

Jump to content

ነፋስ ስልክ

ከውክፔዲያ
ለአዲስ አበባ ሠፈር፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶን ይዩ።
ነፋስ ስልክ

የነፋስ ስልክየእጅ ስልክ ወይም ተንቀሳቃሽ (ሞባይል) ስልክ ሽቦ አልባ በእጅ የሚይዝ ስልክ አይነት ነው። በአሁኑ ዘመን በመላ ዓለሙ ውስጥ የነፋስ ስልኮች ቁጥር ከቆዩት ቤት ውስጥ ቋሚ ባለ ገመድ ስልኮች ቁጥር ይበልጣል። ይህ የሚገርመው የድሮው ቋሚ አይነት ስልኮች ከንፋስ ስልኮች ይልቅ እጅግ ብዙ ዓመታት በገበያው ላይ ኑረዋል፤ ንፋስ ስልኮች ግን ለአጭር ዘመን ብቻ ተገኝተዋል። ስለዚህ በዓለሙ በጠቅላላ የንፋስ ስልክ መስፋፋት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እጅግ ተከናወነ። እንዲህም የሆነበት ሳቢያ የንፋስ ስልክ አገልግሎት ለመክፈት ከቤት ስልክ ይልቅ ቀላልና ርካሽ ሆኗል። የዛሬ ንፋስ ስልኮች ደግሞ በአንድ ጊዜ ብዙ ተጨማሪ ችሎታዎች ሊያስገኙ ይችላሉ፤ ከነዚህም ውስጥ ጽሑፍን ማሳየትና መላክ፣ ስዕልን ማሳየትና መላክ፣ ቪዴዮን ከድምጹ ጋራ ማሳየትና መላክ፣ ቴሌቪዥን ማሰራጨትና የኢንተርኔት ግንኙነት ማቅረብ አሉ፤ ይህም ሁሉ በአንድ ትንሽ መሣርያ ሲሆን ከዚህ በላይ እንደ ካሜራ ፎቶዎች ወይም ፊልም ማንሣት ያስችላሉ። ይህም በእንግሊዝኛ እስማርት ፎን የሚባለው መሣሪያ ነው።

በዓለሙ የንፋስ ስልኮች ቁጥር እየበዛ ሲሆን፣ በአንዳንድ አገራት እንኳን መጠኑ ከሙላት በላይ ደርሶአል፤ ለምሳሌ በ2000 ዓ.ም. በአውሮፓ ህብረት አገራት በአማካኝ ለመቶ መኖሪያዎች 119 ነፋስ ስልክ ግንኙነቶች ነበሩ።[1] ዘመናዊ ንፋስ ስልኮች የሚሰጡት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት ከማናቸውም ሌላ ዘዴ ጋር ይወዳደራል። በተለይ ብዙ ለሚዘዋወሩ፣ በመደሰቻ ቦታ ላሉ ወይም ቋሚ የቤት ኢንተርኔት ግንኙነት ለሌላቸው ተጠቃሚዎች እንደ ኢንተርኔት በር ያገልግላሉ።

  1. ^ Tinet 2009 እ.ኤ.አ.፣ ከአውሮፓ ኮሚሽን ሪፖርት Archived ኖቬምበር 14, 2013 at the Wayback Machine (እስፓንኛ)